የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ | Federal Document Authentication And Registration Agency |DARA|

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ከታች ይመልከቱ
የማህበራት /ኃ.የተ. የግ. ወይም አክሲዮን/ መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ማረጋገጥ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. በማህበሩ ባለድርሻዎች ተቀባይነት ያገኘ ረቂቅ መመሥረቻ ጽሁፍ እና ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ማቅረብ፤
  2. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ የማህበሩን ስም ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ፤
  3. የአገልግሎት ክፍያ መክፈል፣
  4. የማህበሩ ባለድርሻዎች እና ሥራ አስኪያጅ በአካል መቅረብ፤
  5. የማህበሩ ባለድርሻዎች እና ሥራ አስኪያጅ መታወቂያ ማቅረብ፤
  6. የማህበሩ አድራሻ የኪራይ ቤት /ህንፃ/ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ውል ማቅረብ።
ማስታወሻ
  • አስፈላጊ ሰነዶች ሁሉ ተሟልተው ሲቀርቡ ሁሉም ባለድርሻዎች በተቋሙ ኦፊሰር ፊት እየቀረቡ በመተዳደሪያ ደንቡ እና መመስረቻ ፅሁፉ ላይ ይፈርማሉ።,
  • የማረጋገጥ እና ምዝገባ ሂደት ሲጠናቀቅ፣ መተዳደሪያ ደንቡ እና መመስረቻ ፅሁፉ በተቋሙ የተረጋገጠ እና የተመዘገበ ህጋዊ ሰነድ ይሆናል።

የመኪና፣ የሞተር ሳይክል፣ የመኪና አካላት፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ሽያጭ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/፤
  2. የሻጭና የገዥ መታወቂያ፤
  3. ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
  4. የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
  5. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
ማስታወሻ
  • በውክልና ከሆነ ሰነድን ለማረጋገጥ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማረጋገጫ ዋና እና ከዋና ጋር የተመሳከረ ቅጂ።
  • ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
  • ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
  • ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
ቤት፣ የሊዝ መብት ወይም ሌሎች ንብረቶች |Other Assets| በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የተዋዋዬች መታወቂያ፤
  2. ሻጭ/የስጦታ ሰጪ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፤
  3. የሻጭ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
  4. ስሪቱ ነባር የሆነ የሻጭ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፤
  5. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
ድርጅት |Enterprise| በሽያጭ ለማስተላለፍ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የዋና ንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
  2. የሻጭ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
  3. የገቢዎች ክሊራንስ፤
  4. ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፤
  5. የንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፤
  6. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
  7. የሻጭ፣ የገዥ/የስጦታ ተቀባዩ መታወቂያ፤
  8. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
የቤተሰብ ውክልና ለመስጠት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የወካይ/የወካዮች/ መታወቂያ፤
  2. የስጋ ዝምድና መኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
  3. የሚወካከሉት ባልና ሚስት ከሆኑ የጋብቻ ማስረጃ፤
  4. በውክልና ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ ዝርዝር የንብረት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ፤
አጠቃላይ ልዩ/ውስን/ ውክልና ለመስጠት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የወካይ/የወካዮች/ መታወቂያ፤
  2. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ፤
  3. ከንግድ ማህበራት ውጭ የሆኑ ሌሎች ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
  4. በውክልና ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ ዝርዝር የንብረት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ፤
ለጠበቃ ውክልና ለመስጠት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የወካይ/ዮች መታወቂያ፤
  2. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ፤
  3. ከንግድ ማህበራት ውጭ የሆኑ ሌሎች ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
  4. የጥብቅና ፈቃድ ቁጥር፤

ማሳሰቢያ
በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።

በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

Comments

Popular posts from this blog

የአሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን | Driver and Vehicle Licensing and Control Authority