ለንግድ ማህበር ቲን ለማውጣት
ለግለሰብ ንግድ ድርጅት ቲን ለማውጣት
ለድርጅት ሰራተኛ ግለሰብ ቲን ለማውጣት
የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ለመቀበል
ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ
ለተርን ኦቨር ታክስ ለመመዝገብ
ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ለማቅረብ
ለግብር ከፋይ ድርጅት የሚጠቅሙ መረጃዎች
IFRS ለማስተግበር
አገልግሎት የሚሰጥባቸው ፅ/ቤቶች
- ለኃላ. የተ. የግል ማኅበራት እና ለአክሲዮን ማኅበራት - በገቢዎች ሚኒስቴር ሥር የፌዴራል የታክስ ጽ/ቤቶች፤
- ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ አመታዊ የሽያጭ ገቢ ለሚያገኙ ቢዝነሶች - የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጽ/ቤት፤
- ከ5 ሚሊዮን እስከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ አመታዊ የሽያጭ ገቢ ለሚያገኙ ቢዝነሶች - የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፤
- ከ1 ሚሊዮን እስከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ አመታዊ የሽያጭ ገቢ ለሚያገኙ ቢዝነሶች - አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፤
- ከ500,000 ብር እስከ 1 ሚሊዮን ብር አመታዊ የሽያጭ ገቢ ለሚያገኙ የግል ንግድ ባለቤቶች - በክልል የገቢዎች ባለሥልጣን ሥር የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት፤
- ከ500,000 ብር በታች አመታዊ የሽያጭ ገቢ ለሚያገኙ የግል ንግድ ባለቤቶች - በክልል የገቢዎች ባለሥልጣን ሥር የወረዳ ጽ/ቤት።
ለንግድ ማህበር ቲን ሰርተፊኬት ለማውጣት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
በክፍለ ከተማ የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ፦
- የመጠየቂያ ቅጹን መሙላት፤
- በውልና ማስረጃ የፀደቀ የማህበሩ የመመስረቻ ፅሁፍ ማቅረብ፤
- ስራ እስኪያጅነትን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ፤
- ስራ አስኪያጅ አሻራ መስጠት፤
- ስራ አስኪያጁ ፎቶ መነሳት፡፡
ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃዎች
- ለግል ንግድ ስራ የንግድ ባለቤቱ ያመለክታል፤
- ለማህበራት (ኃላ. የተ. የግል ማኅበር ወይም አክሲዮን ማኅበር) ሥራ አስኪያጅ ያመለክታል፤
- ባለቤቱ ወይም ማህበሩ ሥራ ባይጀምርም እንኳን ታክስ (በየወሩ፣ በየሩብ አመቱና በየአመቱ) የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት።
ለግለሰብ ንግድ ድርጅት ቲን ሰርተፊኬት ለማውጣት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
ለድርጅት ሰራተኛ /ግለሰብ/ ቲን ለማውጣት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
በክፍለ ከተማ የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ፦
- የመጠየቂያ ቅጹን መሙላት፤
- ከሚሰራበት ድርጅት ሰራተኛነቱን የሚገለፅ እና ቲን እንዲያወጣ የሚጠይቅ ደብዳቤ ማቅረብ፤
- አሻራ መስጠት፤
- ፎቶ መነሳት፡፡
የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ለመቀበል
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
- የታክስ ከፋዩ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው በጹሁፍ ጥያቄ ማቅረብ አለበት፣
- የታክስ ከፋዩ ውዝፍ የታክስ እዳ ወይም ወቅታዊ የታክስ ክፍያ የፈጸመ መሆን አለበት፣
- የታክስ ከፋዩ ውዝፍ የታክስ እዳ ወይም ወቅታዊ የታክስ እዳ ለመክፈል የክፍያ ስምምነት የገባና በውሉ መሰረት እየከፈለ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ፣
- በደረሰው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ላይ ቅሬታ ያለው ታክስ ከፋይ በታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ የስራ ክፍል ወይም ይግባኝ ሰሚ ኮሚሺን ወይም በየደረጃው ለሚገኝ ፍርድ ቤት ቅሬታውን አቅርቦ በመታየት ላይ የሚገኝ ስለመሆኑ የፁሁፍ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
ማስታወሻ
- የታክስ ክሊራንስ የሚጸናው ለቢዝነስ ለአንድ አመት ነው፤
- ለንብረት ማስተላለፍ ሲሆን የታክስ ክሊራንስ የሚጸናው ለሶስት ወር ነው፤
- የታክስ ክሊራንስ የሚፀናበትን ጊዜ ማራዘሚያ መጠየቅ ይቻላል።
ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ
- በአመት ውስጥ 1 ሚሊዮን ብር ወይም ከዚያ በላይ አመታዊ የሽያጭ ገቢ ያላቸው ቢዝነሶች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብሳቢነት ይመዘገባሉ፤
- ከቢዝነስ ደንበኞቹ 75% ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት ለተ.እ.ታ. የተመዘገቡ ከሆነ ድርጅቱ በፈቃደኝነት ለተ.እ.ታ መመዝገብ ይችላል፤
ማስታወሻ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ በማናቸውም የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ጠቅላላ ሽያጭ ብር 70,000,000(ሰባ ሚሊዮን) እና ከዚህ በላይ ለሆነ ታክስ ከፋይ እያንዳንዱ ወር ሪፖርት ማድረግ፤
- በማናቸውም የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ጠቅላላ ሽያጭ ከብር 70,000,000(ሰባ ሚሊዮን) በታች የሆነ ታክስ ከፋይ የ3 ወር ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበዎታል።
- አመታዊ የሽያጭ ገቢን መነሻ በማድረግ ቢዝነሱ ከተርን ኦቨር ታክስ ወደ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም በግልባጩ ለመቀየር መጠየቅ ይችላል፡፡
ለተርን ኦቨር ታክስ ለመመዝገብ
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ለተርን ኦቨር ታክስ ይመዘገባሉ።
ማስታወሻ
- አመታዊ የሽያጭ ገቢን መነሻ በማድረግ ቢዝነሱ ከተርን ኦቨር ታክስ ወደ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም በግልባጩ ለመቀየር መጠየቅ ይችላል፡፡
ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ለማቅረብ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
- የአመቱን Z - REPORT
- ዓመታዊ ማሳወቂያ ቅጽ ከደንበኞች አገልግሎት በመውሰድ፣
- Withholding tax ተሰብሳቢ ካለዎት excel summary እና ኦርጅናል ደረሰኝ፣
- የካሽ ሪጅስተር ጥያቄ ካልዎት ዝርዝሩን የሚያሳይ አባሪ፣
- አመታዊ ሪፖርት ላይ ያለው ገቢ እና Z-REPORT ካለው ገቢ ልዩነት ካለው ዝርዝር ማብራሪያ፣
- የየወሩን የተ.እ.ታ ወይም ቲኦቲ እንዲሁም ኤክሳይስ ታክስ ካለ የሽያጭ መጠን የሚያሳይ ዝርዝር በ excel፣
- የ12 ወር የቲኦቲ ወይም ቫት የሽያጭ መጠን እና አመታዊ ማሳወቂያ ቅጽ ከተገለጸው የገቢ መጠን ልዩነት ካለው ዝርዝር ማብራሪያ ከነአባሪው፣
- የወጭ ዝርዝር ደረሰኝ፣
- CGS የተሰራበት ዝርዝር መረጃ፣
- የሂሳብ ሌጀር፣
- የቋሚ ንብረት ደረሰኝ ወይም ማስረጃ የድርጅቱ ስም/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለበት NB አመታዊ ሂሳብ መግለጫ ይዘው ሲቀርቡ የሂሳብ ባለሙያ ሰው ቢሆን ይመረጣል።
ለግብር ከፋይ ድርጅት የሚጠቅሙ መረጃዎች
ግብር ከፋዮች ንግድ ፍቃድ ካወጡ በኋላ ምን ማድረግ አለባቸው?
- የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ወዲያውኑ መግዛት፤
- ደረሰኝ ከማሳተምዎ በፊት ለማተሚያ ቤት የህትመት ፍቃድ ከገቢዎች መውሰድ፤
- ማንኛውም ለግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገበ ድርጅት ከ3,000 ብር በላይ አገልግሎት ከ10,000.00 ብር በላይ የዕቃ ግዥ የፈፀመ እንደሆነ በፈፀመው ግዥ መጠን ቅድመ ታክስ ግብር /ዊዝሆለዲንግ/ በመቀነስ ማሳወቅ፤
- ቅድመ ታክስ ግብር /ዊዝሆለዲንግ/ ግዥ ከተፈፀመበት ወር ቀጥሎ ባለው ወር ገቢውን ማሳወቅ፤
- ንግድ ፍቃድ ካወጡ ከቀጣይ ወር ጀምሮ የተርን ኦቨር ታክስ /TOT/ በየወሩ ሪፖርት ማድረግ፤
- አመታዊ የሽያጭ ገቢያቸው ከ500,000 ብር በታች የሆኑ የግል ንግድ ባለቤቶች በየአመቱ በሚያገኙት የሽያጭ ገቢ ግምት ላይ የሚታሰብ ታክስ ያሳውቃሉ፤
IFRS ለማስተግበር
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
- ለመጨረሻ ግዜ ኦዲት የተደረገ የሂሳብ መግለጫ ወይም ለመጨረሻ ግዜ የቀረበ የሂሳብ መግለጫ ኮፒ፤
- ኦዲት ያደረገው ወይም ሂሳቡን ያዘጋጀው ድርጅት ሰርተፊኬት ኮፒ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ፤
- የንግድ ስራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ኮፒ፤
- መተዳደሪያ ደንብ ኮፒ፤
- መመስረቻ ጽሁፍ ኮፒ።
ማስታወሻ
- ከተራ ቁጥር1-6 ከጀርባው የድርጅቱን ማህተም ማድረግ፤
- ተቋሙ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት እና የስራ አስኪያጅ ወይም የተወካይ ፊርማ አርፎበት ገጾቹ ላይ ከፊት ለፊት ማህተም አድርጎ ወደ ተቋሙ ማምጣት፤
- በውክልና ከሆነ የውክልና ደብዳቤና መታወቂያ ኮፒ መቅረብ ይኖርበታል።
- የተቋሙ አድራሻ:- 6ኪሎ ሊደርሺፕ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 437, 438 እና 443
- ቀደም ሲል ወደ ተቋሙ በመምጣት ምዝገባ ያደረገ የሪፖርት አቅራቢ አካል በIFRS የተዘጋጀ የሂሳብ መግለጫ ለማህተም ወደ ተቋሙ ማምጣት እንደማያስፈልግና IFRSን ያልተገበረ ደግሞ ተቋሙ በከለሰው የትግበራ ግዜ 2015/2016 በIFRS የተዘጋጀ ሪፖርት ለተቋሙ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።
በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።
Comments
Post a Comment