የአሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን | Driver and Vehicle Licensing and Control Authority

የአሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ከታች ይመልከቱ

የቦሎ አገልግሎት ለማግኘት

ቦሎ የማስደረግ ሂደት

  1. የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ማስደረግ፤
  2. የመንገድ ፈንድ ክፍያ መፈፀም፤
  3. አሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅ/ጽ ቤት ያለውን ሂደት በመፈፀም ቦሎ መውሰድ።

ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች

  1. የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/፤
  2. ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ከፈፀሙበት ተቋም የሚሰጥ የምርመራ ሰነድ፤
    1. የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ የተገባበት ሰነድ፤
    2. የመንገድ ፈንድ የተከፈለበት ሰነድ፤

    ተጨማሪ

    1. ለግል ንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ በንግድ ፈቃዱ ስም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ፤
    2. ለንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ በተሽከርካሪው ሰሌዳ፣ የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ።

    ማስታወሻ

    • ሊብሬው በዕዳ የታየዘ ከሆነ ከአጋጁ የተፃፈ የስምምነት ደብዳቤ መቅረብ አለበት፤
    • የተሽከርካሪ ምርመራ ሲያስደርጉ፣ የምርመራ ሰነዱ በተቋሙ ሁለት ቴክኒሺያኖች እና በተቋሙ ሃላፊ መፈረም አለበት፤
    • በተሽከርካሪ ምርመራ ወቅት ተሽከርካሪው ወደ ምርመራ ተቋሙ መምጣቱን የሚያረጋገጥ የተሸከርካሪውን ሰሌዳ በግልፅ የሚያሳይ ፎቶ በምርመራ ሰነዱ ላይ መያያዝ አለበት፤
    • ለአዲሰ አበባ ሰሌዳ፣ ምርመራ ከተደረገ 20 ቀን ማለፍ የለበትም፤
    • ለኢቲ ሰሌዳ ምርመራ ከተደረገ 30 ቀን ማለፍ የለበትም፤
    • ተሽከርካሪው ያለፈውን ዓመት የቴክኒክ ምርመራ ያላደረገ ከሆነ ቅጣትን ጨምሮ የዘመኑን የቦሎ ምርመራ ክፍያ ይፈፅማሉ፤
    • ቦሎ ማድረግ ባለቦት ቀን ሳያደርጉ ከቀሩ ለዘገዩበት እያንዳንዱ 15 ቀን የአንድ መቶ ብር ቅጣት ይከፍላሉ፤
    • ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የኮድ ሁለት የአካል ጉዳተኞች ከሆነ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    ለአዲስ ተሽከርካሪ የኮድ 2 /የቤት/ ሰሌዳ ለማውጣት

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፤
    2. የዲክላራሲዮን ሙሉ ሰነድ በማቅረብ፤
    3. ተሽከርካሪው ለጭነት አወሳሰን የነጠላ ክብደት መመዘን የሚገባው ከሆነ የተመዘነበት ማረጋገጫ ሰነድ /የሚዛን ወረቀት/፤
    4. ተላላፊ ሰሌዳ በመውሰድ ተሽከርካሪውን በአካል ወደ ፅ/ቤቱ በማምጣት ለቴክኒክ /Specification/ ምርመራ ማቅረብ፤
    5. ለፅ/ቤቱ ተላላፊ ሰሌዳውን መመለስ፤
    6. በፅ/ቤቱ ባለሙያዎች የአዲስ ተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ ማስደረግ፤
    7. 2% የቴምብር ቀረጥ ክፍያ መፈፀም፤
    8. ለተሽከርካሪው የተገባ የሶስተኛ ወገን የመድህን ዋስትና ሰነድ፤
    9. ለተሽከርካሪው ፍጥነት መገደቢያ መገጠሙን የሚያረጋግጥ ከፌደራል ትራንሰፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተፃፈ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ፤
    10. የተሽከርካሪው ባለቤት ስድስት ወር ያልሞላው ሁለት ጉርድ ፎቶ፤
    11. ቴምብር፤
    ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች እና ክፍያዎች ሲያሟሉ ፅ/ቤቱ ሰሌዳ፣ ቦሎ እና ሊብሬ ይሰጥዎታል።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    የተሽከርካሪ ባለቤት ስም ዝውውር ለመፈፀም

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. የተሽከርካሪውን ሊብሬ ማቅረብ፤
    2. የባለንብረቱ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ፤
    3. ሽያጭ የሚፈፅመው የባለንብረቱ ተወካይ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ውክልና ማቅረብ፤
    4. ሻጭ እና ገዢ በፅ/ቤቱ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ፎርም ሞልተው መፈራረም፤
    5. የተሽከርካሪው ዋጋ ግምት ከፅ/ቤቱ መቀበል፤
    6. በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ /ውልና ማስረጃ/ የተረጋገጠ የሽያጭ ውል ማቅረብ።
    7. ገዢ ግለሰብ ከሆነ የገዢ ስድስት ወር ያልሞላው ሁለት ጉርድ ፎቶ፤
    8. ቴምብር፤
    9. የአገልግሎት ክፍያ።

    ማስታወሻ

    • ከአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰጠ የተሽከርካሪ ዋጋ ግምት ሰነድ፤
    • ተሽከርካሪው ኮድ 3 ከሆነ ከገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰጠ ከግብር ነፃ መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ /ክሊራንስ/፤
    • ሻጭ እና ገዢ ግለሰቦች ከሆኑ የሁለቱም የቀበሌ መታወቂያ፤
    • የተሽከርካሪውን ዋጋ ግምት መሰረት ያደረገ የሽያጭ ግብር ክፍያ፤
    • የአገልግሎት ክፍያ።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    የተሽከርካሪ ሰሌዳን ከኮድ 2 ወደ ኮድ 3 ለማስለወጥ

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. ባለንብረቱ የቀበሌ መታወቂያ ዋናውን ከኮፒ ጋር ማቅረብ፤
    2. የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፤
    3. ጉዳዩን የሚፈፅመው ተወካይ ከሆን በውልና መስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና የተወካይን መታወቂያ ከኮፒ ጋር ማቅረብ፤
    4. የቴክኒክ ምርመራ ሰነድ ማቅረብ፤
    5. ለኮድ 3 የሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና የተገባበት ሰነድ ማቅረብ፤
    6. በኮድ 2 የተሰጠውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ መመለስ፤
    7. ቴምብር፤
    8. የአገልግሎት ከፍያ መፈፀም።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    የተሽከርካሪ ሰሌዳን ከኮድ 3 ወደ ኮድ 2 ለማስለወጥ

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. ባለንብረቱ የቀበሌ መታወቂያ ዋናውን ከኮፒ ጋር ማቅረብ፤
    2. የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፤
    3. ጉዳዩን የሚፈፅመው ተወካይ ከሆን በውልና መስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና የተወካይን መታወቂያ ከኮፒ ጋር ማቅረብ፤
    4. የቴክኒክ ምርመራ ሰነድ ማቅረብ፤
    5. ለኮድ 2 የሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና የተገባበት ሰነድ ማቅረብ፤
    6. በኮድ 3 የተሰጠውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ መመለስ፤
    7. ከገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰጠ ከግብር ነፃ መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ /ክሊራንስ/ ማቅረብ፤
    8. ቴምብር፤
    9. የአገልግሎት ከፍያ መፈፀም።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    በጠፋ ሊብሬ ምትክ ለማውጣት

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፤
    2. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
    3. ሊብሬው ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
    4. ተገቢውን ክፍያ እና ሂደት በመፈፀም ሊብሬው ስለመጥፋቱ በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማስወጣት፤
    5. ማስታወቂያው አየር ላይ ለ15 ቀን ከቆየ በኋላ ጋዜጣውን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማቅረብ፤
    6. የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    በጠፋ ወይም በተበላሸ ቦሎ ምትክ ለማውጣት

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፤
    2. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
    3. የተሽከርካሪው ሊብሬ፤
    4. ለጠፋ ቦሎ ከሆነ ቦሎው ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
    5. ለተበላሸ ቦሎ ከሆነ የተበላሸውን ቦሎ፤
    6. የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    የተሽከርካሪ ታርጋ ከክልል ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. መኪናው ተመዝግቦ ካለበት ፅ/ቤት የዝውውር ቅፅ ተሞልቶ በፖስታ ታሽጎ ለተቀባይ ፅ/ቤት በፖስታ ማስላክ
    2. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
    3. ተሽከርካሪውን ለፅ/ቤቱ ባለሙያ እይታ በአካል ማቅረብ፤
    4. የተሽከርካሪውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ ማስረከብ፤
    5. ለአገልግሎት ተገቢውን ክፍያ መፈፀም፤
    6. ምትክ ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ መረከብ።

    ማስታወሻ

    • ፖስታው ከመላኩ በፊት የዝውውር ጥያቄው በትክክለኛ የዝውውር ቅፅ መሞላቱን ማረጋገጥ፤
    • የተቀባይ ፅ/ቤት ትክክለኛ የፖስታ አድራሻ መሆኑን ማረጋገጥ፤
    • የፋይል ዝውውር ቅፁ ከተሞላ ስድስት ወር ከሞላው ቅፁ ተቀባይነት ስለማይኖረው ቅፁ በተሞላ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቀባይ ፅ/ቤት በመቅረብ ጉዳዩን ማስፈፀም፤

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    መንጃ ፈቃድ ለማውጣት

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. የፅሁፍ እና የተግባር ፈተና ማለፍ፤
    2. ዕጩ አሽከርካሪው የቀጠሮ ወረቀት ማቅረብ፤
    3. ከማሰልጠኛ ተቋሙ የሰልጣኝነት መታወቂያ ማቅረብ፤
    4. የዕጩ አሽከርካሪው የመታወቂያ ኮፒ፤
    5. ዕጩ አሽከርካሪው በአካል መገኘት፤
    6. የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    መንጃ ፈቃድ ለማደስ

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው መንጃ ፈቃድ፤
    2. የጤና ማስረጃ ከተፈቀደላቸው ተቋማት፤
    3. የአገልግሎት ክፍያ ስድስት መቶ ሃያ (620.00) ብር።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    በጠፋ መንጃ ፈቃድ ምትክ ለማግኘት

    ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

    1. መንጃ ፈቃዱ ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
    2. የባለጉዳዩ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት፤
    3. የአገልግሎት ክፍያ።

    ↑ ወደ ማውጫ ተመለስ


    ማሳሰቢያ

    በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።

    በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

    Comments

    Post a Comment

    Popular posts from this blog

    የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ | Federal Document Authentication And Registration Agency |DARA|