የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ | Immigration Nationality & Vital Events Agency |INVEA|
የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ከታች
ይመልከቱ
የፓስፖርት አገልግሎቶች
የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች
አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
የአገልግሎት ሂደት
- ቀጥሎ ባለው ድህረገፅ ላይ በመመዝገብ ቀጠሮ ያስይዙ፤ https://www.ethiopianpassportservices.gov.et/
- ቀጠሮውን በሞሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ለአገለግሎቱ መክፈል የሚገባዎትን ክፍያ በባንክ ይክፈሉ፤
- በቀጠሮዎት ቀን ከታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ይዘው ወደ ተመዘገቡበት የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በአካል ይሂዱ፤
ቀጠሮ ለማስያዝ ከባለጉዳይ የሚጠበቁ
- የቀበሌ መታወቂያ፤
- የልደት ሰርተፊኬት፤
- በባንክ የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
ማስታወሻ
- በድህረ ገፁ ላይ ቀጠሮ የማስያዝ ሂደቱን ከመጀመርዎ በፊት የቀበሌ መታወቂያ እና የልደት ሰርተፊኬትዎን በሶፍት ኮፒ ስካን አድርገው ያዘጋጁ
- ቀጠሮ ሲያሲዙ ከድህረ ገጹ የሚያገኙትን ባር ኮድ ያለው የቀጠሮው ማጠቃለያ |Application Summary| ፕሪንት አድርገው ያስቀምጡት።
በቀጠሮዎት ቀን ማሟላት ያለብዎት ነገሮች
በቀጠሮዎት ቀን ወደ ኢምግሬሽን እና ዜግነት ጉዳይ መስሪያ ቤት ሲሄዱ ከታች የተዘረዘሩትን አሟልተው ይሂዱ፦
- ለፓስፖርት ዕድሳት ከሆነ የቀድሞውን ፓስፖርት ይያዙ፤
- ቀጠሮ ሲያሲዙ ከድህረ ገጹ የሚያገኙትን ባር ኮድ ያለው የቀጠሮው ማጠቃለያ |Application Summary|፤
- የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ኮፒ ጋር፤
- የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ከአንድ ኮፒ ጋር።
ማስታወሻ
- ፓስፖርት የሚወጣለት 18 ዓመት ያልሞላው ልጅ ከሆነ ልጁ በአካል መገኘት አለበት።
- በመተጨማሪ ከልጁ ወላጆች አንዳቸው የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመያዝ በአካል መገኘት አለባቸው።
ፓስፖርትዎ መድረሱን ለማወቅ
- ቀጥሎ ያለውን ድህረገፅ ይክፈቱ https://www.ethiopianpassportservices.gov.et/#/Status
- የፓስፖርት ቀጠሮ ሲያሲዙ የተሰጠዎትን የምዝገባ ቁጥር /Application Number/ እና ባንክ ክፍያ የፈፀሙበት ቁጥር /Order Code/ በሞሙላት የፓስፖርት ቀጠሮዎ የደረሰበትን ሁኔታ ማወቅ ይችላሉ።
ፓስፖርት ለመቀበል
ፓስፖርትዎ ዝግጁ ሲሆን ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በአጭር የፅሁፍ መልክት ፓስፖርትዎን እንዲረከቡ
የሚገልፅ መልዕክት በሞባይል ስልክዎ ይደርስዎታል፤
ፓስፖርቱን ለመቀበል በተቀጠሩበት ቀን እና ቦታ ሲሄዱ የሚከተሉትን ያሟሉ፦
- የቀበሌ መታወቂያ |ዋናውን ከአንድ ኮፒ ጋር|፤
- ባር ኮድ ያለው ቀጠሮ ያስያዙበት ወረቀት።
ማስታወሻ
- ጉዳዮትን የፈፀሙት በክልል ካሉ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ቅርንጫፍ ከሆነ ከዛው ቅርንጫፍ ፓስፖርትዎን ይረከባሉ፤
- ጉዳዮትን የፈፀሙት በአዲስ አበባ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ከሆነ ፓስፖርትዎን የሚረከቡት በኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ድርጅት በኩል ይሆናል፤
- ፓስፖርትዎን የሚረከቡበት ቅርንጫፍ ፓስታ ቤት የስምዎን የመጀመሪያ ፊደልን መሰረት በማድረግ ከታች ከተዘረዘሩት የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች በአንዱ ይሆናል፤
- ፓስፖርት ሲቀበሉ ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ሃምሳ (50.00) ብር ይከፈላሉ።
- በB፣ C እና D የሚጀምሩ ስሞች ከአራዳ ፖስታ ቤት (ፒያሳ) ቅርንጫፍ
- በE እና F የሚጀምሩ ስሞች ከአራት ኪሎ ፖስታ ቤት (ቱሪስት ሆቴል ጎን) ቅርንጫፍ፤
- በG፣ H እና I የሚጀምሩ ስሞች ልደታ ፖስታ ቤት (ልደታ ኮንደሚንየም) ቅርንጫፍ፤
- በJ፣ K እና L የሚጀምሩ ስሞች ልደታ ሰንጋ ተራ ቤት (ሰንጋ ተራ ኮንደሚንየም ወይም ንብ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ጀርባ) ቅርንጫፍ፤
- በN፣ O እና P የሚጀምሩ ስሞች አፍሪካ ጎዳና ፖስታ ቤት (ደንበል አካባቢ) ቅርንጫፍ፤
- በT፣ U፣ V እና W የሚጀምሩ ስሞች ካዛንቺስ ፖስታ ቤት (ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ጀርባ) ቅርንጫፍ፤
- በA፣ M፣ Q፣ R፣ S፣ X፣ Y እና Z የሚጀምሩ ስሞች ዋናው ፖስታ ቤት።
አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት
ከሚከተሉት ምክንያቶች አንዱን የሚያሟሉ ከሆነ ከመደበኛው በተለየ ባጭር ቀናት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ወይም ነባር
ፓስፖርትዎን ማደስ ይችላሉ። ይኸውም፦
- የህክምና ደብዳቤ ካለዎት፤
- ጉዞዎ ለትምህርት ስኮላርሽፕ ወይም ዲቪ ከሆነ፤
- ከባለስልጣን መስሪያቤት የተፃፈ ደብዳቤ ካለዎት፤
- በሌላ ሃገር የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት፤
- ከሌላ ሃገር የተላከ የጉዞ ጥሪ ድብዳቤ ካለዎት፤
- ጉዞዎ ለስራ ጉዳይ የሆነ አስቸኳይ ጉዞ ከሆነ፤
- ጉዞዎ ለበጎ ስራ የሆነ ጉዞ ከሆነ።
ማስታወሻ
- የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጠው አንደ መደበኛው በኢንተርኔት በመመዝገብ አይደለም። ባለጉዳዩ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት ወይም በክልሎች ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት የሚያስፈፅም ይሆናል፤
- የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያ የመደበኛውን ክፍያ እጥፍ ነው፤
- አስቸኳይ ፓስፖርት የሚጠየቀው ለተበላሸ ወይም ለጠፋ ፓስፖርት ከሆነ እና የተበላሸው /የጠፋው/ ፓስፖርት ከስድስት ወር በላይ ቀሪ የአገልግሎት ወራት ከነበረው ፓስፖርቱን ለማውጣት የሚከፈለው ክፍያ ከመደበኛው ክፍያ ሁለት እጥፍ ይሆናል።
የልደት ምስክር ወረቀት ማረጋገጥ
የልደት ምስክር ወረቀት የሚረጋገጠው በኤጀንሲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በምስክር ወረቀቱ ላይ የጀርባው ማህተም
ሲደረግበት ነው።
የጀርባ ማህተሙን ለማስመታት የሚከተለውን ሂደት ይፈፅሙ፦
የጀርባ ማህተሙን ለማስመታት የሚከተለውን ሂደት ይፈፅሙ፦
የአገልግሎት ሂደት
- የልደት ሰርተፊኬቱን ካወጡበት የወረዳ ወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት ኦሪጅናል የልደት ሰርተፊኬቱን በማቅረብ የድጋፍ ደብዳቤ ይውሰዱ፤
- የድጋፍ ደብዳቤውን እና ኦሪጅናል የልደት ሰርተፊኬቱን በመያዝ አዲስ አበባ ከተማ፣ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ፣ በሸገር መናፈሻ ውስጥ ወደሚገኘው የወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት ይሂዱ፤
- በፅ/ቤቱ የተቀመጠውን ሂደት በመፈፀም እና የአገልግሎት ክፍያ በመክፈል የጀርባ ማህተም ያስመቱ።
ማስታወሻ
- የልደት ምስክር ወረቀቱ ከ18 ዓመት በታች ለሆነ ልጅ ከሆነ፣ ከወረዳ ወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት የሚሰጠውን ደብዳቤ ከወላጆች እንዳቸው ወይም ህጋዊ ሰነድ ያለው አሳዳጊ ሊጠይቅ ይችላል።
ማሳሰቢያ
በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።
በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።
Comments
Post a Comment