የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት | Ethiopian Electric Utility
የሚሰጡ አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ከታች
ይመልከቱ
አዲስ ቆጣሪ ለማስገባት
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ
- የቀበሌ መታወቂያ እና የመታወቂያ ፎቶ ኮፒ፤
- አንድ ጉርድ ፎቶ፤
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የህንፃ ካርታ፤
- የሽያጭ ውል፣ የውርስ ሰርተፊኬት፣ የፅሁፍ ኑዛዜ ቃል ወይም ሰርተፊኬት ከሚመለከተው የመንግስት አካል (ደብዳቤ)፤
- የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የዋስትና ማረጋገጫ (ያለመቃወም) ደብዳቤ እና የመጨረሻ የኪራይ ክፍያ ሰነድ ከኪራይ ውል ጋር፤
- የይዞታ ባለቤትነትን በተመለከተ ክርክር ሲኖር ከሚመለከተው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ፤
- የንግድ ተቋም ከሆነ የንግድ ፈቃድ፤
- የመንግስት /የቀበሌ/ ቤት ከሆነ ከመንግስት የተሰጠ ደብዳቤ ወይም የኪራይ ውል፤
- ለቢል ቦርድ፣ ለማስታወቂያ አገልግሎት ከተጠየቀ ከክፍለ ከተማ ወይም ከወረዳ አስተዳደር የፍቃድ ደብዳቤ ማቅረብ፤
- የሽርክና ድርጅት ከሆነ የሽርክና ማቋቋሚያ ደብዳቤ፤
- ካርታ ለሌላቸው የከተማ ቦታዎች ከክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ የተሰጠ ደብዳቤ፤
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሌላቸው አመልካቾች የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ 3 ምስክሮች መታወቂያቸውን በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቀረብ ተቃዋሚ ቢመጣ ያለማስጠንቀቂያ ቆጣሪው የሚነሳ ለመሆኑ ይፈርማሉ።
- ለገጠር ቦታዎች ከመንግስት አካል የተሰጠ ባለቤት ስለመሆኑ የሚገልፅ ደብዳቤ (የይዞታ ካርታ አያስፈልግም)፤
- ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ከሆነ የምስረታ ሰርተፊኬት፣ የመመስረሻ አንቀፅ፣ የዳይሬክተሮች ዝርዝር አድራሻ እና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መታወቂያ፤
- የቀረበው የኃይል ጥያቄ ከ7.5 ኪሎ ዋት በታች ከሆነ ባመልካቹ በራሱ የቀረበ የቦታ ዝግጁነት ረፖርት፤
- ከ7.5 ኪሎ ዋት በላይ በአንድ (1) ቆጣሪ ለሚጠይቁ ደንበኞች
- አቅራቢያው ያለው ትራንስፎርመር የሚችል ከሆነ የውስጥ ኤሌክትሪክ ዝርጋታ ንድፍ (ኢንስታሌሽን ፕላን)፣
- የስራ ማጠናቀቂያ ሪፖርት (ካለ)
- የምርመራ ሰርተፊኬት፤
- የታደሰ ፍቃድ ባላቸው ባለሙያዎች የተሞላ የመስሪያ ቤቱ ቅፅ።
የቆጣሪ ባለቤት ስም ዝውውር
- የሽያጭ፣ የውርስ፣ የስጦታ ማስረጃ (ለማመሳከሪያ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፤
- አንድ ጉርድ ፎቶ፤
- መታወቂያ (ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፤
- ለመጨረሻ ጊዜ (የቅርብ ጊዜ) የከፈሉበት ቢል ፎቶ ኮፒ።
የቆጣሪ ማሻሻያ
- አንድ ጉርድ ፎቶ፤
- መታወቂያ (ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፤
- ለመጨረሻ ጊዜ (የቅርብ ጊዜ) የከፈሉበት ቢል ፎቶ ኮፒ።
ቆጣሪ ለማዞሪያ
- አንድ ጉርድ ፎቶ፤
- መታወቂያ (ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፤
- ለመጨረሻ ጊዜ (የቅርብ ጊዜ) የከፈሉበት ቢል ፎቶ ኮፒ።
የውል ማስረጃ ለሚፈልጉ
- መታወቂያ (ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፤
- ቀድሞ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል የገባው ደንበኛ ህጋዊ ውክልና ወይም የውርስ ሰነድ፤
- ለመጨረሻ ጊዜ (የቅርብ ጊዜ) የከፈሉበት ቢል (ለማመሳከሪያ ዋናውን) ከፎቶ ኮፒ ጋር።
ማሳሰቢያ
በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።
በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።
Comments
Post a Comment