የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር | Ministry of Trade and Industry

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ከታች ይመልከቱ
የንግድ ሰራ ለመጀመር
አዲስ የንግድ ድርጅት አቋቁመው ወደ ስራ ለመግባት ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሂደት ተከትለው ምዝገባዎችን መፈፀም ይጠበቅብዎታል። ይኸውም፦
የድርጅት ስም ምዝገባ መፈፀም
በውልና ማስረጃ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ማረጋገጥ
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማግኘት
የንግድ ምዝገባ መፈፀም
የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት
የንግድ ፈቃድ ማግኘት
የድርጅት ስም ምዝገባ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ መሙላት፤
  2. የቢዝነስ ባለቤት (ለኃላ. የተ. የግል ማ./ለአክሲዮን ማኅበር) ለኩባንያው ሥም ሶስት አማራጮች ማቅረብ፤
  3. የአገልግሎት ክፍያ መክፈል።
ማስታወሻ
አመልካቹ ካቀረቡት ሶስት የስም አማራጮች በሌላ ድርጅት ያልተያዘ አንድ ስም ከተገኘ ይኽ ስም ለአመልካቹ በደብዳቤ ተገልፆ ይሰጠዋል። ነገር ግን የቀረቡት ሶስቱም ስሞች የተያዙ ከሆኑ አመልካቹ ሌላ አማራጭ ስም እንዲያቀርብ ይጠየቃል።
አዲስ የንግድ ምዝገባ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፤
  2. የአመልካች/የሥራ አስኪያጁ ወይም የወኪሉ/ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /የሚሰራ ፓስፖርት /የመንጃ ፈቃድ /የመሥሪያ ቤት መታወቂያ /ፎቶኮፒ።
ማስታወሻ
  • አመልካቹ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ የኢንሸትመንት ፈቃድ፤
  • በውክልና ከሆነ ሰነድን ለማረጋገጥ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማረጋገጫ ዋና እና ከዋና ጋር የተመሳከረ ቅጂ።
የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ ወይም ስረዛ
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
  1. ማሻሻያ የሚደረግባቸውን ማስረጃዎች/በህግ አካል የጸደቀ ዋና ቅጂ ቃለ ጉባኤ፤
  2. አዲሱ አባል የህግ ሰውነት ያለው አካል ከሆነ የዚሁ አዲስ አባል የመመሥረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና እና ኮፒው፤
  3. የመቋቋሚያ የምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ ሰነድ እና አዲስ በሚቋቋመው ማህበር ውስጥ ለመግባት ሥልጣን ባለው የማበሩ አካል መወሰኑን የሚያሳይ አግባብነት ባለው የኢትዮጵያ ሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ ጉባኤ ወይም ደብዳቤ፤
  4. ማህበሩ የውጭ ሀገር ማህበር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወይም አባል ሆኖ አክስዮን እንዲገዛ የተፈቀደበት ደብዳቤ፤
  5. ማሻሻያው የካፒታል ከሆነ እና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ የባንክ ማስረጃ፤
  6. የስራ አስኪያጅ ለውጥ ከሆነ የሚተካው ስራ አስኪያጅ የቀበሌ መታወቂያ /ፓስፖርት /የመንጃ ፈቃድ /የመሥሪያ ቤት መታወቂያ ከፎቶ ኮፒው ጋር፤
  7. ቀደም ብሎ የተሰጡ የንግድ ስራ ፍቃዶች ተመላሽ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
  8. የንግድ ስም ምስክር ወረቀት ተመላሽ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
  9. የማህበሩ ስረዛ ወይም ማሻሻል የሚገልጽ በሰነድ የተረጋገጠ ቃለ ጉባኤ ዋና ቅጅ፤
  10. ኦዲት ሪፖርት።
አዲስ ንግድ ፈቃድ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. የብቃት ማረጋገጫ ለሚጠየቅባቸው ዘርፎች፣ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት።
የንግድ ፈቃድ እድሳት
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. ኦዲት ሪፖርት፤
  2. ከሚመለከተው አካል የግብር ክሊራንስ።
ማስታወሻ
ደንበኞች በኦንላይን አገልግሎት የንግድ ፈቃዳቸውን በየዓመቱ ማደስ ይችላሉ።
የንግድ ስራ ፈቃድ ማሻሻያ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. ማሻሻያ የሚደረግባቸውን ማስረጃዎች፤
  2. በህግ አካል የጸደቀ ዋና ቅጂ ቃለ ጉባኤ።
ማስታወሻ
ደንበኞች በኦንላይን አገልግሎት የንግድ ፈቃዳቸውን ማሻሻል ይችላሉ።
የንግድ ስራ ፈቃድ ስረዛ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. ከሚመለከተው አካል የግብር ክሊራንስ።
ማስታወሻ
ደንበኞች በኦንላይን አገልግሎት የንግድ ፈቃዳቸውን መሰረዝ ይችላሉ።
አዲስ የንግድ ስም መጠየቅ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. የአመልካቹ/የሥራ አስኪያጁ 6 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተነሳው ፓስፖርት መጠን ያለው ጉርድ ፎቶ ግራፍ።
ማስታወሻ
ደንበኞች በኦንላይን አገልግሎት አዲስ የንግድ ስም መጠየቅ እና ከንግድ ፈቃዳቸው ጋር ማያያዝ ይችላሉ።
የንግድ ስም ማሻሻያ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
  1. ማሻሻያ የሚደረግባቸውን ማስረጃዎች፤
  2. በህግ አካል የጸደቀ ዋና ቅጂ ቃለ ጉባኤ።
ምንጭ፦
ማሳሰቢያ
በዚህ ፅሁፍ ላይ የሚቀርበውን መረጃ በተቻለ መጠን ትክክለኛ እንዲሆን እንጥራለን። ነገር ግን ይህን ፅሁፍ በመጠቀምዎ ለሚደርስብዎ ማንኛውም ጉዳት ወይም መጉላላት ሃላፊነት እንደ ማንወስድ እባክዎን ይወቁልን።

በዚህ መረጃ ላይ ክፍተት ካገኙ አሊያም ተጨማሪ መረጃን ሊሰጡን ከፈለጉ እባክዎን ከታች ባለው አስተያየት መስጫው ሳጥን ያስፍሩለን። ስለ ትብብርዎ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

Comments

Popular posts from this blog

የአሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን | Driver and Vehicle Licensing and Control Authority

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ | Federal Document Authentication And Registration Agency |DARA|